About Us
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው
የተከበራችሁ ዑለማዎች ዱዓቶች ፣ ኡስታዞች ፣ ወንድም እህቶች ፣ አባቶች እናቶች በኸይር ስራ ላይ አብራችሁን የነበራቹ በሙሉ ላለፉት ስድስት አመታት በተለያየ መልኩ በአፍሪካ ቲቪ ሂባ ቲዩብ እንዲሁም በጀይሉ ቲቪ የሚድያ ስራ እንቅስቃሴዎች የምታውቁኝ ወንድማቹህ ሙባረክ አደም ከሚድያው ስራ ጎን ለጎን አቅሜ ያገራልኝን የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ስሳተፍ ቆይቼያለሁ። በእነዚህ ስድስት አመታት ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በመዘዋወር በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተጎዱ የህብረተሰባችንን ክፍሎች አቅም በፈቀደ መልኩ በሚድያ ያገኘሁትን ተቀባይነት በመጠቀም የተለያዩ በጎ አድራጊ ግለሰቦችን እና ተቋማትን በማስተባበር ለተፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ ለመሆን ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ። በዚህ ሂደት ውስጥ በርካታ ወንድምና እህቶቼ በገንዘብ በጉልበት በእውቀት እንዲሁም በሀሳብ ከጎኔ ሆነው በርካታ ስኬቶችን መጎናፀፍ ችለናል።
በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች ሁለት የብሎኬት እና ሁለት የጭቃ የገጠር መስጂዶችን መስራት ችለናል።
ከ 58 በላይ የውሃ ጉድጓድ ማስቆፈር ችለናል
ከ10 በላይ የቲም ልጆችን የትምህርት ወጪን በመሸፈን ማስተማር ችለናል።
ለ 5 መስጂዶች የምንጣፍ ፣የሶላር መብራት እና ስፒከር ማስገጠም ችለናል።
ከተለያዩ በጎ አድራጊዎች በተገኘ ድጋፍ ለተከታታይ 5 ዓመታት የረመዷን ፃም ማፍጠሪያ አስቤዛ ድጋፍ ማድረግ ችለናል፤የኡድሁያ እርድ ማከናወን ችለናል።
ከ 5000 በላይ ቁርዓንን በተለያዩ አቅጣጫዎች በመጓጓዝ ለመስጂዶች እና መድረሳዎች ማድረስ ችለናል።
በህመም ላይ ለሚገኙ የተለያዩ ወገኖቻችን ገንዘብ በማስተባበር ወደ ውጭ ሄደው እንዲታከሙ ማድረግ ችለናል።
በየዓመቱ በተለያዩ አከባቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መስጠት ችለናል።
እንዲሁም ሌሎች በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን የስራዬ ደጋፊ እና አጋዥ ከሆኑ ወንድም እህቶቼ ጋር መስራት ችለናል። ሆኖም ይህንን የተሳካ እና አላህ ዘንድ የተወደደን ስራ ሰፊ ትኩረት እና ግዜ በመስጠት ድርጅታዊ መዋቅርን በጠበቀ መልኩ ለማከናወን ያስችለን ዘንድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የእስላማዊ ድርጅት ፍቃድ በመውሰድ በተሻለ መልኩ ስራችንን አስፍተን ለመስራት ቢሮ በመከራየት እና ቢሮውን በማደረጃት ስራችንን በይፋ ጀምናል። አልሀምዱሊላህ
በዚህ መሰረት 10 የጠቅላላ ጉባዔ እና 5 የቦርድ አባላት ያለው አደረጃጀት ፈጥረናል።
እስከዛሬ ድረስበተለያየ መልኩ ከጎናችን የነበራችሁ ግለሰቦች እና የበጎ አድራጎት ድርጅት አመራሮች ከዚህም በኃላ በሰፊ ልንሰራ ባሳብነቸው እቅዶች እና ክንወኖች ላይ ከጎናችን በመሆን የበኩላችሁን ኃላፊነት አቅማችሁ በቻለው መንገድ ሁሉ እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
በስተመጨረሻም በተባበረ ክንድ የማህበረሰባችንን ችግር ለመፍታት በምናደርገው ጉዞው ውስጥ የሚጣልብንን አማና እና ኃላፊነት በአግባቡ እንድንወጣ አላህ ያግዘን ዘንድ በዱዓችሁ አትርሱን ለማለት እንወዳለን።
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየታችሁ ወይም ድጋፋችሁ 0921125054 0937060707
በአካል ለመጎብኘት ቤተል ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት MK ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ታገኙናላችሁ ወሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
How do we work?
Shaped by decades of experience within Haiti's communities and with its educators, we affect change by bringing together real-world solutions, policy expertise, sustainable financing and collaborative partnerships.
Technology & Innovation
To make a lasting impact, we know that we must actively engage and include the communities we are seeking to help. We are continually learning and growing in how we show up as an authentic, ethical partner.
Finance & Investing
Utilizing and adapting technologies familiar to the developed world, we can provide teachers, parents, and students with products and services to improve learning and decision-making.
Partnering with Local Communities
By nurturing relationships with likeminded organizations and private individuals, we're able to unlock new sources of capital and scale up our work far beyond what traditional funding can do alone.
Our team
ስራ አስኪያጅ
ስልክ +251937060707 / +251921125054 / +251113491473
hibafoundation2024@gmail.com
ቤተል ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት MK ህንፃ 1ኛ ፎቅ